ሶስት መንትያ ፍቅረኛሞች ያሉት አነጋጋሪው ጉደኛ ዩቲዩበር – The youtuber who marry a triplets

ሰላም ውድ የሁሉ ዴይሊ ቤተሰቦች እንደምን ቆያቹህ ሰላምታችን በያላቹህበት ይድረስልን ። በዛሬው ፕሮግራማችን ለናንተ የያዝናችህ ከሀገራችን ባህል እና ማንነት አንጻር ወጣ ያለ እና ብዙወች ጉድ ያስባለውን አስገራሚ የፍቅር ግንኙት ሲሆን ሶስት መንትያ ከእህትማማቾችን ጋር የፍቅር ግንኙነት የጀመረው እና ለማግባት በዝግጅት ላይ ያለውን አንድ አነጋጋሪ ግለሰብ የምነግራቹህ ይሆናል

ተመሳሳይ መንትያ እህትማምቾችን ያፈቀረው ኬኒያዊ ስቴቮ ይባላል ። በሀገረ በኬንያ Comrades Triplets በመባል የሚታወቁት ሶስት እህትማማቾችን ማለትም ኬት ፣ ሔዋን እና ሜሪ በትውልድ ሀገራቸው የመዝናኛ ፕሮግራሞች ላይ ርዕሶችን ሆነው ቆይተዋል ። እነዚህ መንታ እህትማማቾች የሚያገባው ይህ ግለሰብ ሶስት ፍቅረኞች ወይንም ደግሞ የትዳር አጋሮች መኖራቸው ምንም ችግር የለውም በማለትም ነው የሚገልጸው ። መንትያ እህትማማቾች ኮምራደስ ትሪፕሌት በሚባል የራሳቸው ዩቲብ ቻናል ላይ ስቴቮ ደግሞ ኮምራደስ ፍላቮር በሚባል ዩቲብ ላይ ቻለንጆን እና አዝናኝ የሆኑ ቪዲወችን የሚሰሩ ታዋቂ የሆኑ ሰዎችም ናቸው ። ስቴቮን ለመጀመሪያ ግዜ ያወቀችው ኬት የምትባለዋ ስትሆን ኮማንደር ፍላቮር በሚለው ዩቱብ ቻናሉ ላይ የሚሰራቸው ስራወቹን በማየት ሲሆን ከዛ በኋልም በደንብ መተዋወቅ እና በአካል ለመገናኘት ያበቃቸው ። ከእርሷ ጋር በመተዋወቅ ላይ እያሉም ነበር ስለ ሁለቱ መንትያ እህትማማቾቿ መናገር የጀመረቸችው ። ቀስ በቀስ ወደ እርሱ ሁሎችም ቀረቡ ከዛም አልፎ መገናኘት ነበር የጀመሩት ። ወደ እሱም ቀርበው ከሦስቱም ጋር የፍቅር ግንኙነት እንዲኖረዉ ፈቃደኛ መሆኑን ይጠይቁታል ፡፡ እርሱፍ ቃደኛ ሆነላቸው ። ሁሎችም አንድ አይነት ፍላጎት እና ሀሳባቸው ስልነበር ከዚህ ሰው ጋር በፍቅር ውስጥም ወደቁ ። በንግድ ስራ ተሰማርቶ የሚሰራው ስቴቮ የፍቅር ግንኙነቱ በሂወታቸው ላይ ችግር እንደማይፈጥርም ተናግሯል ።

ሶስቱ መንትያ እህትማማቾች ስቴቮ ቆንጆ እንደሆነ ቢያስቡም በተለያዩ አጋጣሚዎች ሳያውቁት በፍቅር መውደቃቸውን ተናግረዋል ። ከአጋራቸው ጋር የሚያሳልፉበት ሰአታቶች እና ቀናቶችንም የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት ነው እየተጠቀሙ ያሉት ።ከእያንዳንዳንዳቸ ጋር ሰኞ ፣ ማክሰኞ እና ረቡዕ በቅደም ተከተል ግዜያቶች የሚያሳልፍ ሲሆን አርብ ላይ ደግሞ ላይ በጋራ አንድ ላይ ግዜያቶቻቸውን የሚያሳልፉበት ቀን እንደሆነ ነው የተናገረው ። ሦስታችንም እንበቃዋለን እንጂ ሌላ እንዲያመጣ አንፈቅድም፡ ደስተኛ ቤተሰቦች እንሆናለን በማለት እህትማማቾች ተናገራዋል ። እህትማማቾቹ ስለጋብቻቸው እና ልጅ ስለ የመውለድ በጋራ እቅዶቻቸውን እንዳወጡ ነው ከመረጃወች ይገልጻሉ ። ፍቅር ለአንድ ሴት ልጅ ብቻ እንዳልሆነ እና እኔ ከአንድ እና ከሁለት በላይ ሚስት አግብቼ መኖር እንደምፈልግ አስብ ነበር ይላል ስቴቮ ። ከዚህ በፊትም የቀድሞ ጓደኞቼ ትተውኝ የሄዱት አንድ እና ከዛ በላይ ሚስቶችን ማግባት እንደምፈልግ ስነግራቸው ባለመስማማታቸው ነው ይባላ ። ለኬት ፣ ለሔዋን እና ለሜሪ በተደረገ ቃለ ምልልስ መጀመሪያ ላይ ከሦስቱም አንዷ ዕድለኛ የሆነችውን ስቴቮን በቅርብ ጊዜ ለማግባት እንዳቀዱ ነበር የተናገሩት በኋላ ነገሩ ሁሉ ተቀያየረባቸው እንጂ ። በተመሳሳይ ጊዜ ከሶስት ሴቶች ጋር መገናኘት ምንም አዲስ እና ትልቅ ነገር እንዳልሆነ ነው የሚናገረው ።

ሦስቱም ከአንድ ሰው ጋር ሲገናኙ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የተናገሩት መንትዮች በዚህ ድርጊትም ከሀገሪቱ በአንዳንድ ማህበረሰቦች ዘንድ የተለመደ ነው በማለት ይገልጺታል ። ሶስቱ መንትያ እህትማማቾች የማይነጣጠሉ በመሆናቸው አንድ አይነት ሰው ማግባት እንደሚፈልጉ ምናልባትም በሂወት እስካሉ ድረስ አንድነታቸውን ወደ ፊት መቀጠል እንደሚችሉ ነበር የነገሩት ። በሀገረ ኬኒያ የመጀመሪያ ታሪክ የሰራም ይህ ግለሰብ የሚያስደንቀው ነገር መጀመሪያ ያውቃት ከነበረችው ውጭ ያሉት እህትማማቾች ጸባያቸው ፡ ቁንጅናቸው ተመሳሳይ በመሆኑ አንዷን ብቻ መርጦ ለማግባት ተችግሮ ስለተቸገረ ከሶስቱ ጋር አብሮ መኖር ወስኗል ። ከልጅነታችን ጀምሮ ሕይወታችን ተመሳሳይ ነው አሁንም ተመሳሳይ መሆን አለበት በማለት ነው እያንዳንዳቸው የሚናገሩት ። እህትማማቾችም መጀመሪያ ላይ እንቆቅልሽ ነበር የመሰለን ከግዜያት በኋላ ግን ምንም ነገር ሊያግደን አልቻለም፡ በአንድ ባል ተሳስረናል በማለት በደስታ ነው የተናገሩት ። ግለሰቡ እንደሚለው ከሆነ አንድ ነገር ለማግኘት የግድ አንድ ነገር ማጣት አለብን እኔም ይህንን ነው ያደረኩት ይላል ። በአፍሪካዊ ባህላችን ጋር የማይሄድ ይህ ጋብቻ መጥፎ ቢሆንም አንዳቹ ተደስተውበታል አንዳንቹ ደግሞ ተናደውበታል ይላል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *