የኢንስታግራም ሞዴሎች በዱባይ የሚሰሩት አስደንጋጭ ጉድ ወጣ

ዘመኑ የቴክኖሎጂ እንደመሆኑ መጠን ዓለማችን በማህበራዊ ድረ-ገጾች ዙሪያ እንደምትሽከረከር የሚካድ ነገር የለም፤ ስለዚህም በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እንደ የሙሉ ጊዜ ሥራ የማህበራዊ ሚዲያ ሰራን እየሰሩ ነው። ኮከብ የመሆን፣ ታዋቂነት ለማግኘት እና ብዙ ገንዘብ የማፍራት እድል እንዳለ በማመናቸው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪ መሆን የጀመሩ ወጣቶች ቁጥራቸው እየጨመረ ነው።

ለዚህም ስራቸው ዋነኛው ግብአት ደግሞ የሚያምር እና ለእይታ ሳቢ የሆኑ ቦታዎች ላይ ፎቶ መነሳት እና ቪድዮ መቅረጽ ነው ። ይህንንም ተከትሎ  ብዙዎቹ ዓመቱን በሙሉ የተለያዩ ቦታዎች ይጓዛሉ ። ከዚህም ውስጥ አንዷ እና ዋነኛዋ በብዙዎች ተመራጭ የሆነቸው ዱባይ ናት።  እንደ እውነቱ ከሆነ ዱባይ በፍጥነት የአለም ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ዋና ከተማ ሆናለች፣ ብዙ የኢንስታግራም ሞዴሎች ምርጥ የፎቶ ቀረጻ እድሎችን ለመፈለግ ወደዚያ እየበረሩ ነው።

ነገር ግን፣ ይህን ለማድረግ ከፍተኛ ወጪ ያስወጣል ታዲያም ከነዚ ምርጥ ምስሎች ጀርባ ያለውን ታሪክ በግልጽ ሲናገሩ አይታይም፣ ስለዚህ ጉዳይም ለማወቅ ብዙዎች ይጓጓሉ ፡ ለምንድነው የኢንስታግራም ተፅእኖ ፈጣሪዎች ሁል ጊዜ ወደ ዱባይ የሚሄዱት? ወደ ዱባይ ስለሚጓዙት የኢንስታግራም ሞዴሎች በስተጀርባ ያለው አስደንጋጭ እውነት በዛሬው ፕሮግራማችን ከተለያዩ አለም አቀፍ ጋዜጦች አጠናቅረን ይዘንላቹህ መጥተናል አብራችሁን ቆዩ።

ለምንድነው ሴት ኢንስታግራም ተጽኖ ፈጣሪዎች ሁል ጊዜ ወደ ዱባይ የሚሄዱት?

ወደ አስደንጋጮቹ ምክንያቶች ከመግባታችን በፊት፣ በጣም መሠረታዊ በሆነው ማብራሪያ እንጀምር፡ እሱም ቱሪዝም ነው ። ዱባይ ቀዳሚ ከአለማችን የቱሪስት መዳረሻዎች ውስጥ አንዷ ናት። በዘመናዊ አርክቴክቸር እና አዝናኝ የሽርሽር ጉዞዎች፣ ቱሪዝም ለከተማዋ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ መሆኑ ምንም አያስደንቅም።

እንዲሁም ዱባይ የተንደላቀቀ የአኗኗር ዘይቤን ለሚመኙ እና ያንን ከፍሎ ማጣጣም ለሚፈልጉ በጣም ጥሩ እና ምቹ  ነው። የኢንስታግራም ተፅእኖ ፈጣሪዎች ሁል ጊዜ ተከታዮቻቸውን ለማብዛት እና ተጽኗቸውን ለማስፋት በዛ ላይ ከዚ ከተጽኖ ፈጣሪነታቸው ጋር ተያይዞ በሚያጋጥማቸው እድሎች በመጠቀም ከፍተኛ ገንዘብ ወደሚጠይቁት የቅንጦት ስፍራዎች ያቀናሉ ልምዳቸውንም  ለሁሉም ይካፈላሉ።

ወደ ሃገራችን ስንመጣ ደግሞ አሁን አሁን በኢንስታግራም ታዋቂ የሆኑ ቆነጃጂት ሴት ኢትዮጵያዊያን መቁጠር ከባድ ነው ከነዚህ ዝነኛ የኢንስታግራም ሞዴሎች ውስጥ ደግሞ ዱባይ ሳይዝናና የመጣ መፈለግ በጣም አዳጋች ነው ። ምንም ኢትዮጵያዊነት ጨዋነት ነው ብንል ገንዘብ ደግሞ ሰውን ሊያስደርገው የሚችለው ነገር በጣም ብዙ ነው። እነዚህ ታዋቂ የእንስታግራም ሞዴሎች ደግሞ በዱባይ የሚዝናኑባቸው ቦታዎች በጣም ውድ ከመሆናቸው የተነሳ እራሳቸው ይህንን ክፍያ ይችላሉ ማለት ይከብዳል ።

ከሃገራችን ስንወጣ ደግሞ የዚህ የኢንስታግራም ጉድ እንደቀጠለ እናገኘዋለን ። ውጪ ሃገረ ያሉትስ ገንዘብ አላቸው እራሳቸውን በደንብ ማዝናናት ይችላሉ ብለን በናስብም እውነቱ ግን ይሄ አይደለም፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ወደ ዱባይ የሚሄዱበት ምክንያቶች ከዚያ የበለጠ አስደንጋጭ ነው።

ለአብዛኛው አለም ኢንስታግራም ሰዎች ህይወታቸውን በኢንተርኔት ላይ እንዲካፈሉ የሚያስችል የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ነው፣ነገር ግን ለተፅእኖ ፈጣሪዎች እና ሞዴሎች ለወጣት እና ማራኪ ሴቶች ከባለጸጋ ወንዶችን ትኩረት የሚያገኙበት ቦታ ሆኗል። ብዙ የኢንስታግራም ሴት ተጸኖ ፈጣሪዎች ከሀብታሞች ጋር ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ ወደ ዱባይ ያቀናሉ።

እ.ኤ.አ. በ 2018 ኮስሞፖሊታን ዩኬ የተባለው ታዋቂው የእንግሊዝ የመዝናኛ ሚድያ በዱባይ ያሉ ተፅእኖ ፈጣሪዎች ላይ ዘገባ ሰርቶ ነበር ። ሚድያውም በዘገባውም ማሪያና የተባለች በስራዋ ተርጓሚ የሆነች አነጋግሯል ፣ እሷም በዱባይ ከተማ ውስጥ ስላሉት የተጽዕኖ ፈጣሪዎች ህይወት ጠንቅቃ ታውቃለች ። ማሪያና ስለ ዱባይ እንዲህ ብላለች: – “ወንዶች እርስዎ ሊገምቱት ለማትችሉ ነገሮች ሳይቀር ብዙ ገንዘብ ያወጣሉ “የሜክሲኮ የእጽ ነጋዴዎችን  ያስታውሰኛል – ብርቅዬ የሆኑ እንስሳትን እና በወርቅ ያጌጡ ሽጉጦችን በመግዛት እና በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ባማውጣት ሴቶችን ከእነሱ ጋር ለመዝናናት ይከፍላሉ. ወንድሜ እንኳን ወደ እሱ ምግብ ቤት ሄደው ፎቶግራፎችን እንዲለጥፉ ከ Instagram ላይ ያገኛቸውን ልጃገረዶችን ይከፍላል.”

ኮስሞፖሊታን ዩኬ የተባለው ታዋቂው የእንግሊዝ የመዝናኛ ሚድያ  በተጨማሪም የኢንስታግራም ሞዴሎች ውበታቸውን እና ወጣትነታቸውን በመጠቀም ብዙዎች ለመድረስ ብቻ የሚያልሙትን የአኗኗር ዘይቤ እንደሚኖሩት  ጽፏል። አንቶኒ ከለንደን የተባለ ሰው ይህን በቱጃሮች እና በኢንስታግራም ሞዴሎች የሚደረገውን ስምምነት  “የቅንጦት ቅምጦች” ሲል ይገልጸዋል። 

አንቶኒዮም ሲቀጥል ለነዚህ ሚልየነር ደንበኞቼ ምርጥ ቆነጃጂት አሉን ያለ ሲሆን  በየትኛውም ቦታ ላሉ ደንበኞቼ በሚፈልጉ ግዜ ጠረጴዛቸው ድረስ 10 ውብ ቆነጃጂቶች እንዲመጣላቸው አደርጋለው ይላል። ሴቶቹ ማድረግ የሚጠበቅባቸው ቆንጆ ሆነው እንዲታዩ ብቻ ነው። ብልጥ እና ነገሩ የገባቸው ከሆነ ደግሞ ከማህበራዊ ሚዲያ እና ድግስ ብዙ ገንዘብ ማግኘት ይችላሉ ።

ውድ ተመልካቾቻችን እስካሁን ያለውንም ሰምተው ጉድ የጉድ አለም እያሉ ይሆናል ነገሩ ገና አልተጀመረም ከዚህም የባሰ አስደንጋጭ ነገር በዱባይ በኢንስታግራም ተጽኖ ፈጣሪ ሴቶች እየተካሄደ ነው ። ምንጩ ያልተነገረ መረጃ አስደንጋጭ ጉድ አውጥቷል ከዚም ውስጥ እነዚህ ታዋቂ የኢንስታግራም ሞዴሎች በሴተኛ ዳሪነት ንግድ በዱባይ ከፍተኛ የሆነ ገቢ እያገኙ መሆኑን እና ብዙዎችን የሚያማልለው ፎቶዎቻቸው እና ቅንጡ ቦታዎች በዚሁ የሴተኛ ዳሪነት ንግድ ገቢ ምንጭ እንደሆነ የሚዝናኑት የማይናቁ ብዙ መረጃዎች እየወጡ ነው።ምንጩ ኮስሞፖሊታን ዩኬ የተባለው ታዋቂው የእንግሊዝ የመዝናኛ ሚድያ ሲዘግብ፣ “በተለይ ሴቶች ከሀብታም የዱባይ ሼኮች የተለያዩ ቦታ እየሄዱ መዝናናት የተለመደ ነው ሲል ዘግቧል ፣ በምላሹም በፆታዊ እና ወሲባዊ ድርጊቶች ውስጥ እንዲሳተፉ ይጠይቃሉ። ከእነዚህ ወሲባዊ ድርጊቶች ውስጥ አንዱ በጣም ዘግናኝ በሆነ መልኩ በተለይ ይህን በሚያዩበት ጊዜ እየተመገቡ ከሆነ ፣ ራቅ ብለው ይመልከቱ – ከዚህ አጸያፊ ድርጊቶች ውስጥም በሚያሳዝን ሁኔታ ሴቶቹ ላይ መጸዳዳትን ያካትታል። ለእንደዚህ አይነት ድርጊት ከ26,000 ዶላር በላይ እንደሚከፍሏቸው ነውም የተነገረው ። 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *