በፖሊሶች የታጀበው አስገራሚው የፖሊሷ ሰርግ – Ethiopia Police Wedding

 ብዙወቹ በተሰማሩበት የሙያ ዘፍር ላይ ጠንካራ ሰራተኛ የሆኑ በተቋማቸው ዘንድ የተመሰገኑ እንዲሁም ደግሞን በህዝብም ዘንድ ታላቅ ክብር የሚሰጣቸው ጥንዶች በተቋማቸው ድጋፍ እና እገዛ ደማቅ የሆነ የሰርግ ስነ ስር አታቸውን ያካሂዷሉ ።

ሰሞኑንም በድሬዳዋ ፖሊስ የተካሂደውን እና የፖሊስነት የደንብ ልሷን ለብሳ ያገባቸው ሙሽራ ብዙወችን አስገርሟል ። በድሪዳዋ ፖሊስ በድምቀት ያገባችው የፖሊስ አባል ዋና ሳጅን ገነት አሎቤ ትባላለች ። በድሪዳዋ ፖሊስ ላለፉት ዘጠኝ አመታት ያክል በተለያዩ የስራ ዘርፎች በፖሊስነት ሞያ አገልግላለች ።

አሁን ላይም በተቋሙ የሪከርድ እና ማህደር ክፍሉ ውስጥ በባለሞያ እያገለገለች ትገኛለች ። ዋና/ሳጅን ገነት በያዝነው በዚህ አመትም አንድ ውጥን ይዛም ነበር ። የራሷን ቤተሰብ ትመሰርት ዘንድ ከፍቅረኛዋ ጋር በትዳር ልትጣመር ጎጆዋን ልትቀልስ ነበር ያሰበችው ። በእዚህ የሀሳብ ውጥን ውስጥ እያለችም ነበር የድ/ዳ ፖሊስ በለውጥ ሪፎርም ከሰራቸው የልማት ተግባራት እና ፕሮጀክቶች ምርቃት ማግስት ቅድሚያ ለሚያገባ  የፖሊስ አባል በፖሊሳዊ የላቀ ክብር የሚቻለውን ድጋፍ አድርጎ እንደሚድር የተናገረው ።

ይህንንም ተከትሎ እንስቷ የፖሊስ አባል እኔ በተቋሜ በመአረግ ብዳር ምነኛ ደስ ባለኝ ስትል ጥያቄዋን ለተቋሙ አቀረበች ። ተቋሙም ጥያቄዋን በደስታ ተቀብሎ የሰርግ ወጪዋንም ከውስጥ ገቢ በከፊል ደግፎ ለመጀመሪያ ሊባል በሚችል መልኩ በትራፊክ ሞተረኛ ፣ በፈረስ እና በበርካታ የፖሊስ ተሽከርካሪ ታጅባ አግብታለች ። የሰርግ ምሽት የእራት ፕሮግራም በቅርቡ ውብ ተደርጎ ለውጦች በተደረጉበት በድ/ዳ ፖሊስ ዋና ፅ/ቤት መምሪያ ግቢ ተዘጋጅቶ ወዳጅ ዘመድ ጎረቤት ጓደኞች ጥሪ የተደረገላችው እድምተኞች በተገኙበት የፖሊስ አባሏ ዋ/ሳ ገነት አሎቤ በድምቀት ባሳለፍነው ቅዳሜ ግንቦት 20 ቀን 2014 አ.ም ነበር የተሞሸረችው ።  

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *