በቀናት ሚልየኖችን አፈሰች – በኢንተርኔት ቱጃር የሆኑት ኪያ እና ሃና

ሰላም የሁሉ ዲይሊ ቤተሰቦች እንደምን ቆያቹህ ። በዛሬው ፕሮግራማችን ለናንተ የያዝንላቹህ ዘመናዊ የኦን ላይ መገበያያ ቴክኖሎጅወችን በመጠቀም ማለትም NFT ወይንም Anon-fungible token (ነን ፈንጀብል ቶከን) ዲጅታል የስእሎችን በመሸጥ ሚሊየነር የሆነችውን ኪያ ታደለ እና በቢትኮይን ንግድ ሚሊየነር የሆነችውን ሀና ተክሌን ሲሆን አሁን ላይ ሁለቱም ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያገኙ ፤ እንዴት እዚህ ደረጃ  እንደደረሱ የምነግራቹህ ይሆናል ።

 ኢትዮጲያዊቷ ሀና ተክሌ በቢት ኮይን ንግድ ስራ ሚሊየነር የሆነች ባለሀብትም ናት ። አዲስ አበባ አብነት አካባቢ ተወልዳ ያደገች ሲሆን እ.ኤ.አ.ከ2006 ጀምሮ በአጋጣሚ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሂዳ ኑሮዋን በዚያው አድርጋ እየኖረች ትገኛለች ። በሂልኮ የኮምፒተር ሳይንስ ትምህርቷን ተምራለች ። የራሷን ስራ መስራት ትፈልግ ስለነበር በርካታ መጽሐፍትን ሳነብ የሕይወቴን መስመር ቀየርኩም ትላለች ። የሕይወቷን መስመር በትምህርት ብቻ አለመሆኑን ስትረዳ የተለያዩ ነገሮችን በአማራጭነት መመልከትም ጀመረች ። ያኔ እጇ ላይ የነበረው አንዱ ኔትወርክ ማርኬቲንግ ነበር ።

በኔትወርክ ማርኬቲንግ ውስጥ ከገንዘብ በተጨማሪም የአመራር ፣ የተግባቦት ፣ የሽያጭና አስተዳደር ክህሎቶችን ያገኘችበት ሲሆን ማግኘት እና ማጣት ብዙ አስተምሮኛል ትላለች ። 2009 ላይ ግን ይህንን  ስራዋን አቁማ ከሕንድ እቃዎችን እያስመጣች ለቸርቻሪዎች መስጠት የጀመረች ሲሆን በ2015 በመክሰሯ ስራዋን አቆመችው ። ስለዚህ ከ2013 ጀምሮ የልቤን ፍላጎት ይዤ በየቀኑ አዳዲስ የንግድ ሀሳቦችን እመለከት ጀመር ትላችለ ። ባለቤቷ ከሥራ ወደቤት ሲመለስ ያገኘቻቸውን የንግድ ሀሳቦች ትነግረውም ነበር ። የባለቤቷ የዘወትር ውትወታዋ ሲበረታበት አንድ ለሊት ቁጭ ብሎ ማንበብ ጀመረ ። ባነበባቸው ጥናቶች ውስጥ የተሳተፉ ዩኒቨርስቲዎች ፣ የተደረጉ ጥናቶች እና  ቢዝነሱ ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ካሳያት በኋላ ስራውን ጀመረች ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ከቢትኮይን ንግድ ገንዘብ ማግኘት የጀመረች ሲሆን በስድስት ወር ውስጥ አንድ ሚሊዮን ዶላር ማግኘት ችላለች ። 

በዚህ ስራዋም ከ30 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በስራቸው ሚሊየን ዶላር እንዲያገኙ አድርጌላሁም ትላለች ። ከዚያ በኋላም ቢዝነሱ እየሰፋ እና እየተጠቀምኩ መጣሁ በማለት ትገልጸዋለች ። አትችይም የሚሉኝ ሰዎች ሁሌም ለሌላ ተጋድሎ ያነሳሱኛል። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሀገሩን ቋንቋ አትናገሪም ያሉኝ፣ ሴት መሆኔን ያስታወሱኝ ሰዎች በአጠቃላይ ዛሬ ለደረስኩበት አነሳስተውኛል ። ቢትኮይን ልክ እንደ ዶላር እና እንደ ዩሮ ሁሉ ገንዘብ ነው ። ከሌላው ገንዘብ የሚለየው ግን ዋጋው ነው። ዋጋው በየጊዜው ይጨምራል እንጂ አይወድቅም ።  በየግዜው እያደገ እንጂ እየቀነሰ ሲሄድ አይታይም ትላለች ሀና  ። ከአንድ ሰው ወደ ሌላው በቀላሉ ዋጋው ሳይሸራረፍ ማስተላለፍ ይቻላል ። ቢትኮይን ለመላክ የሦስተኛ አካል ጣልቃ ገብነትን አስወግዷል ።  ሰዎች ቢትኮይን ንግድ ላይ የመሰማራት እድል እንዳላቸው አልያም ደግሞ ንግዳቸውን በቢትኮይን መገበያየት መቻል አለባቸውም ትላለች ።

 NFT ወይንም Anon-fungible token (ነን ፈንጀብል ቶከን) መቀየር ወይንም ደግሞ መለወጥ የማይችል ሲሆን የተለያዩ የኪነ ጥበብ ስራወችን ማለትም ቪዲዮወችን ፤ ፎቶወችን፤ አውዲዮወችን በኦን ላይ መሸጥ እና መግዛት የሚቻልበት የመገበያያ  ዘዴ ነው ። አሁን ያለንበት ግዜ ዘመናዊ ቴክኖሎጅ እጅግ የረቀቁበት ወቅት በመሆኑ ብዙወቹ ሰዎች አዳዲስ የንግድ ስራወች በኦን ላይን በመስራት ትርፋም እየሆኑ ይገኛሉ ። ብዙወቹ የዚህን የቢዝነስ አለም በመቀላልቀል ባለሀትን ለመሆን ችለዋል ። ታዋቂ ሰዎች ማለትም አርቲስቶች ስራወቻቸን ወይንም ደግሞ የዲጂታል ስእ ግም ነው ። ሰዎች መሬት ለመግዛት የመሬት ካርታ እንደሚሰጣቸው ሁሉ ይህን የገዙ ሰዎች የራሳቸው የስእሉ የዲጂታልካርታ ባለቤት ይሆናሉ ። አንድ ሰው ብቻ በባለቤትነት የሚይዘውም ነው ። ይህ የዲጂታል ገበያያ ወደ ኪነ -ጥበብ አለም ሲመጣ የብዙወቹን ፍላጎት ያሳካ ሲሆን ብዙ ወደ ቢዝነሱ አለም እንዲገቡ እያደረጋቸው የሚገኝም ነው ። በኔትወርኩ በኩል ስራዎቻቸውን ማጋራት እና መሸጥ ይችሉበታል ።  ከአመት አመት በዚህ የኦን ላይን ስራ ላይ የሚሸጡ ስራወች ዋጋቸው እየጨመረ በመምጣቱ ተጠቃሚወችም ትርፋማ እየሆኑ ይገኛሉ ። የተለያዩ አይነት ያላቸው ፎቶወችን የሚሰሩ ሰዎችም እስከ 63 ሚሊየን ዶላር ወይም በኢትዮጵያ ገንዘብ እስከ 3 ቢሊየን ብር በመሸጥ ያተርፋሉ ። ሞዴል እና ተወናይ ኪያ ታደለ የዚህ የመገበያያ ዘዴ ተጠቃሚ ስትሆን እጅግ የሚያምሩ የኢትዮኢያ የነገስታትን ፎቶወችን በመስራት NFT ወይንም Anon-fungible token (ነን ፈንጀብል ቶከን) በማድረግ በተለያዩ ድህረ ገጾች ላይ እየሸጠች የምትገኝም ናት ። በተዋናይነት እና በሞዴልነት ከሰራች በኋልም ነው ወደ ዚህ የኦን ላይ የቢዝነስ ስራመስራት የጀመረችው ። በዚህ በማህበራዊ ሚዲያ የአንድን ሀገር ታሪክን እና ማንነትን በሚገልጹ ፎቶወች እና ቪዲዮወች እያስተዋወቀችበትም ትገኛለች ።

 እጂግ የሚያምሩ የኢትዮጵያውያን ነገስታቶችን ምስል ለምሳሌ የንጉስ ላሊበላ፣ እየቴጌ ጣይቱ ፣ ሳባ ሰገል ፤ የዩዲት ጉዲትን  ምስሎችን ሰርታለች ፤ በሀገራችን ኢትዮጲያ በተለያዩ አካባቢወች ያሉትን የቀደምት ውዝዋዜች በቪዲዮ ሰርታለች ። አሁን በቅርብ ግዜ ደግሞ በተለያዩ የሀገራችን ገጠራማ ቦታወች ሂዳ የተለያዩ የሰጉር ሰራሮችን እና አይነቶችን በቪዲዮ እና በፎቶ ሰርታለች ። ኪያ ታደለ በብዛት የምታዘጋጃቸው ታሪካዊ በሆኑ ፎቶወቿን የምታገኘው ገቢ እጅጉ እየጨመረም መጥቷል  ።  ኢቲሪየም በተሰኘ የዲጂታል የመገበያያ ገንዘብ 355 ኢቲርየም ያገኘች ሲሆን በዶላር ሲመነዘር 1 ሚልየን ዶላር በላይ ሲሆን በእኛ ሃገር ስንመታው ደግሞ በአስደንጋጭ ሁኔታ 55 ሚልየን ብር በላይ የሚቆጠሩ ገንዘጎችን ማግኘት የቻለች ሀብታም ሆናለች ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *