ፍልቅልቋ አርቲስት ዘነቡ ታደሰ ተሸኘች – ህዝቡ በእንባ ተራጨ- የቀብር ስነ-ስርዓት
በሀገራችን ብዙ ሁለገብ የሆኑ የኪነ ጥበብ ስራወችን የሰራችን በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን እና አድናቆትን ያገኘችው አንጋፋዋ አርቲስት ዘነቡ ገሰሰ በአሳዛኝ ሁኔታ በነበረባት ህመም ምክንያት መያዚያ 16 ቀን 2014 አ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች ። በዛሬው እለት ሚያዝያ 17 ቀን 2014 ዓ.ም በቡልቡላ መድሀኒ አለም ቤተክርስቲያን ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ላይ የቀብር ስነ ስአርቷ ተፈጽሟል ።
አርቲስት ዘነቡ በበርካታ ፊልሞችን እና ቲያትሮችን ሰርታለች ። በቡዙ ስራወቿ ዘንድ ነጻነት ያላት ፡ በብዙወቹ ዘንድ ተወዳጅ የሆነች ፡ አስመስላ ሳይሆን ሆና የምትሰራም ናት ። የራሷ መለያ ባህሪ ያላት ስትሆን ምንም አይነት ስልጠናወችን እና ትምህርቶችን ሳትወስድ ነው በተፈጥሮ በተሰጣት ተሰጦ መስራት የጀመረችው ። ፊልም ለመስራት ፍላጎት ኖሯት ካመነችበት እንጅ ለክፍያ ብላ የማትሰራም ናት ። ለአድናቂወቿ አብዝታ የምትጨነቅ የሀገር ፍቅር ስሜት ያላት ታላቅ አርቲስት ናት ። አድናቂወቿ እንኳን በሄደችበት ቦታ ሁሉ ወይንም ደፍሞ በምትገንባቸው ቦታወች ላይ አክብሮት ቅድሚያ የሚሰጣት ተከብራ እና ተወዳ የምትኖርም ነበረች ። አርቲስቷ በተወለደች በሶስተኛው ወሯ ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ ወላጆቿ ያመጧት ሲሆን ፈረንሳይ ለጋ ሲሆን ነበር ኑሮዋን ያደረገችው ። አንጋፋዋ አርቲስት ዘነቡ ገሰሰ በርካታ ፊልሞችን እና የቴሌቭዥን ድራማዎችን ሰርታለች። ከሰራቻቸው ስራወቿ መካከል ፈታኒ ፡ አያስቅም፤ 300 ሺህ፤ ትህትና፤ በተቆለፈበት ፡ በዓለሜ ፡ በወደው አይሰርቁ እና በሌሎችም እጅግ በርካታ ፊልሞች እና አጫጭር ሲትኮም ድራማዎች ላይ በመስራት በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ዘርፍ ውስጥ ጉልህ ድርሻን የተጫወተች ናት ። ትህትና በተሰኘው ፊልም የጉማ አዋርድ ረዳት ተዋናይ ሽልማትን ማግኘትም ችላለች ።
ለ35 አመታት በኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ውስጥ የራሷን አሻራወችን ያሳረፈች ሲሆን ካላት የኪነ ጥበብ ችሎታ ባለፈ በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተሳትፎ በማድረግም ትታዉቃለች ። ሙያዋን በፍላጎቷ ወዳው እንጂ ለክፍያ ብላ የማትሰራው ናት ።
አርቲስት ዘነቡ በ1950ወቹ አካባቢ በኢሀፓ መንግስት ምክኒያት ታላቅ ወንድሟ ራሳቸው ቤት በር ላይ ተገድሎባትም ነበር ። በዛን ግዜ ቤታቸውን ቀና ለቀን ይፈተሹባቸው ስለነበር በጣም ተቸግረው ቤተሰቦቿ መሰደድ ነበር የሚፈልጉት ። በሚኒሊክ ትምህርት ቤት ተማሪ የነበረች ግዜ ድምጿ ስለሚያምር ተቀጥራ እየተከፈላት ሰርታለች። የኪነ ጥበብ ስራወችን መስራት የጀመረችውም ከዚህ ነበር ። ከአዲስ አበባ ለአባቷ ሳትናገር ተደብቃ ጠፍታ ወደ ኤርትራ አስመራ ላይ በወታደርነት ለማገልገል የሄደች ። የወታደር ኦኬስትራ ሆና ሰሜን ነጸብራቅ የሚባል ልዩ ስም ያለው አገልግላለች ። የማርሽ ባንድ ዘንግ ወርዋርም ነበረች ። በውትድርናው ላይም አራት አመት ማገልገል እንዳለባተና አራት አመት እስኪሞላት ድረስ ልጅ መውለድ እንደማይችል ፈርማ ነበር የገባቸው ። ግን ስራዋን እየሰራች እንደማንኛውም ሰው ግዜዋ ሳይሞላ ነበር ኑሮን መኖር ጀመረች ፡ ልጅም ወለደች ። በግዜውም ስለማይቻል ከስራቸው እንዲባረሩ የተደረገ ሲሆን በሀገራችን ጥገኝነት ይሰጠን የሚል ማመልከቻ አስገብተውም ነበር ። ዘነቡ ሴትም ይሁን ወንድ የምወልደው ወታደር ልጅ እንጅ ፈንጅ አይደለም ብላ በወቅቱ የነግረቻቸው ። በመጨረሻም በማስጠንቀቂያ የመጀመሪያ ልጇን እዛው ወልዳ እንድታሳድ አድርገዋል ። አባቷም ወታደር ስለነበር በ1974 የቀይ ኮከብ ጥሪ ዘመቻ ሲደረግ ነበር ወደ ምጽዋ የሄደው ። አባት እና ልጅም እዛው የተገናኙ ሲሆን ከዛ ውስጥ እንዴ መውጣት እንዳለባት እና አዲስ አበባ መጥታ ትምህርችት መማር እንደምትችል ነበር የነገራት ።
ሙሉ በሙሉ ስራውን ትታም መባረር ፈለገች ። ይህ የሚሆነው ደግሞ ነፍሰጡር ከሆነች ነው ። ሁለተኛ ልጇን እርጉዝ ስትሆን ተባረረች እና ሁለት ልጆቿን ብቻ ይዛም ወደ አዲስ አበባ መጣች ። አስመራ አጠቃላይ አራት አመት ከስድስት ወር ያክል ቆይታለች ። ከአንድ አመት ቆይታ በሁላ በአጋጣሚ የኪነ፡ጥበበ ስራወችን መስራት የጀመረችው ። በራስ ቲያትርም ሁለገብ አርቲስት ሆና ማለትም ድምዳዊ ፤ተወዛዋዥ እና አጃቢ ሆና ነበር የምትሰራው ። ከዚህ በፊት አርትስት ዘነቡ በሂወቷ ላይ ያልጠበቀችው እና 17 አመት ላይ ኦፕሬሽን አድርጋ የዳነችው ህመሟ በድጋሜ እንደተነሳባት ነበር በሚዲያወች ላይ ቀርባ የተናጋረችው ። ይህ ያልጠበቀችው ነገር ቀናቶች ሲሄዱ እያመመማት እና ህመሙ እየቀደም እየጨመረ የሄድባት ነበር ወደ ሆስፒታክ የሄደችው ። በጣም አሟት እና ጡቷ ላይ ቆስሎ ለነበረው ህመሟ ምርመራ አድርጋ ከጨረሰች በኋላ ስብ እንጅ ሊላ ነገር የለም በማለት ነበር ማስታገሻ የተሰጠችው ። በዚህም እንዴት ማስታገሻ ብቻ ይሆናል የሚል ጥያቄም ነበር የጠየቀቻቸው ። ከዚህ ቀጥላም ደግሞ አልሻላት ሲል ወደ ሊላ ሆስፒታል ሂዳ የታየችው ። ዶክተሮችም ህመሟን በማየት ሊላ ላይ በተሰጣት ማስታገሻ አዝነው ህመሟ እንደተቀየረ አይተው በማጽናናት ነበር ተሯሩጠው መህደኒቶችን ያዘዙላት ። ለረጅም ህክምና አገልግሎት የሚጠይቅ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ህክምናዋንም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተከታታትላም ነበር ።
የሁለት ሴቶች እና የሁለት ወንዶች እናት ስትሆን ሁለት የልጅ ልጆችም አሏት ። ባደረባት የጡት ካንሰር ህመም ምክንያት በህክማና ስትረዳ ቆይታ በትናትነው እለት ቡልቡላ በሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች ። ብዙ አመታትን ኑሯ የልጅ ልጆችጇን ትልቅ ቦታ ደርሰው ማየት ትፈልግም ነበር ። ብዙ አመታትን ኑሯ የልጅ ልጆችጇን ትልቅ ቦታ ደርሰው ማየት ትፈልግም ነበር ። የቀብር ስነ ስርአቷም በዛሬው እለት ሚያዝያ 17 ቀን 2014 ዓ.ም በቡልቡላ መድሀኒ አለም ቤተክርስቲያን ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ላይ ቤተሰቦቿ ፡ ወዳጅ ዘመዶቿ እና ጉዳኞቿ በተሰበሰቡበት የቀብር ስነ ሰአቷ ተፈጽሟል።