ሶስት መንትዬ እህትማማቾችን ያገባው ጉደኛ ባል – The man who married three identical siblings

ብዙዎቻችን ትዳር ሲባል ወደ አይምሯችን የሚመጣው የተዋደዱ ጥንዶች አስበውበት እና ተዘጋጅተውበት የሚገቡበት ውህደት ወይንም ጥምረት ሲሆን አንድ ወንድና አንዲት ሴት በጋብቻ አንድ የሚሆኑበትም ነው ። ሀብት ንብረት ማፍራት፣ ልጆች ወልዶ፣ በአንድነት ቤተሰብ መስርቶ የሚኖርበት ትዳር በመተሳሰብ ፡ በመተጋገዝ እና በጽናት ሂወታቸው በጥሩ ሁኔታ የሚመሩበት የሂወት አንዱ መስመርም ነው ። በዛሬው ፕሮግራማችን ግን ለናንተ የያዝናችህ ከሀገራችን ባህል እና ማንነት አንጻር ባልተለመደ መልኩ አለምን ጉድ ስላስባሉት ሁለት አስገራሚ ትዳሮችን ነው። ውድ የሁሉ ዴይሊ ቤተሰቦች እንደምን ቆያቹህ እነዚህ ለማመን የሚከብዱ ሁለት አስደናቂ ትዳሮች አንደኛው ደርዘን ሙሉ ማለትም 12 ሚስቶች አግብቶ በአንድ ጣሪያ ስር እየኖረ ያለ ሌላኛው ደግሞ ለማመን በሚከብድ መልኩ ሶስት መንትያ እህትማማቾችን በአንድ ቀን ያገባውን ጉደኛ ሰው።

በሀገረ ሩዋንዳ የሚኖር አን ቻል መሆኑን እናያለን ። የመጀመሪያ ሚስቱን ያገባው ከ16 አመታት በፊት እንደነበር መረጃዎች የሚገልጹ ሲሆን አሁን ላይ ግን ውስጥ ሌሎች 11 ሚስቶችን አግብቷል ። ይህ ግለሰብ 25 የራሱ ልጆች እንዲሁም 9 የማደጎ ልጆች ያሉት በአንድ ጣሪያ ሁሎችንም አስማምቶ እየኖረ ቤተሰቡን በጥሩ ሁኔታ ማስተዳደር መቻሉ ብዙዎችን አስገርሟል ። ይህ ግለሰብ በእርግጥ ከእንደዚህ አይነት ትልቅ ቤተሰብ ጋር በአስቸጋሪ እና አስደሳች የህይወት ወጣ ውረዶች ውስጥ   የሚኖርም ነው  ።

የታሪኩ በጣም አስገራሚው ክፍል ቤተሰቡ አንድ አይነት ምግብ አብረው የሚመገቡ መሆናቸው ፡ እርስ በእርስ መግባባታቸው ምንም አይነት ግጭት በመሃላቸው አልመፈጠርሩ የሚያስደንቅ ነው ። ከሚስቶች ጋር በሰላም እንደሚኖሩ ጎረቤቶች እና የቤተሰብ አባላት እንደረጋገጠም ከመረጃወች አይተናል ። ባልየው በቤታቸው ውስጥ ሰላም እና ስምምነት እንዲኖር ስለሚያደርግ ግጭቶች፣ ክርክሮች፣ ሁከት እና ማንኛውም ዓይነት መጥፎ ነገሮች እንዳይኖር የቤተሰብ አባሎቹን ያያል ይመለከታል ።

በዚህ በደስታ እና በፍቅር ከ12ቱ ጋር አብሮ የሚኖር ሲሆንን እቅዱ የነበረው 20 ሴቶች አብቶ መኖር  ነበር ። ከእያንዳንዳቸው ሚስቶቿ ከአምስት አመት ጀምሮ እስከ 10 አመትድረስ አብረው መኖር  የጀመሩት  ናቸው ። በሀገራችን ይህንን ነገር  ስናየም በአንድ ጣሪያ ስር  እንኳን ለሚኖሩት  ለአንድ ባል  እና ሚስቶች  ከባድ  በሆነበት ግዜው  ይህ የዚህ ግለሰብ ትልቅ  የሆነ የቤተሰብ አባሉ  እርስ በእርሳቸው ተስማምተው   እና  ተረዳድተው እንዲኖርይ ያደረገም ነው። 

አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን ያውም መንትያ እትህማማቾችን በሀገራችን ኢትዮጲያ ያውም በአንድ ቀን ሲያገባ ማየት የተለመደ ነገር አይደለም ተደርጎም አያቅም ይሁን እንጂ በሀገር ኮንጎ ግን አንድ ግለሰበ  ሶስት መንትያ እህትማማቾን በአንድ  ቀን በማግባቱ መነጋገሪያ ሆኗል ። በ2019 ሳአሜንዳ ሲናር የተባለ አንድ የኡጋንዳ ግለሰብ በአንድ ቀን እና በአንድ ድግስ ሶስት ሴቶችን  አግብቷል።

ያገባቸው ሴቶች ሁለቱ የ24 እና የ20 አመት እህታማሞች ፤መሆናቸው በብዙወች ዘንድ ግርምትን የፈጠረ ሲሆን ሶስቱን በተለያየ ሰርግ ለማግባት አቅሜ አይፈቅድም ነገር ግን በአንድ ሰርግ እና በአንድ አዳራሽ ሶስቱንም ማግባቴ እኩል ለሶስቱም ቦታ እንዳለኝ ያሳያል ማለቱ አነጋጋርም ሆኖ ነበር ። በተመሳሳይ በዘንድሮው አመትም ሶስቱን መንትያ እህትማማቾች በአንድ ቀን ፡ በአንድ ድግስ እና  በአንድ አዳራሺ ያገባው ግለሰብም ሉዊዞ ይባላ  ። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደቡብ ኪቩ ውስጥ በካረን የምትኖረው የ32 አመቱ ግለሰብ ሉዊዞ ናታሊ፣ ናዴጌ እና ናታሻ የተባሉትን የሶስት መንትያ እትህማማቾችን አግብቷል ።

በመጀመሪያ ከመንትያ እህትማማቾች አንዷን በማህበራዊ ሚዲያ ማለትም በፌስቡክ አግንቶ እንዳወራት እና ከተወሰነ ግዜ በኋላ ፍቅር እንደያዘው ይናገራል ። እርሷም እሷግሩም ናት ፣ ውበቷን እንኳን መቋምቋም አልቻልኩም እያለ ነው የሚናገረው ። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በአካል ለተከታታይ ግዜያት መገናኘታቸው ሲቀጥልም ናታሊ ወደፊት ምን እንደሚጠብቅህ እና ምን እንደሚያጋጥምህ አታውቅም ማለት ስለ እህቶቿ ናዴጌ እና ናታሻ መልካምነት አወራችው ከዛም አልፎ አስተዋወቀችው ።

የሠርጋቸውን ቀን እና ሌሎች ጉዳዮችን ለመወያየት ናታሊ በምትኖርበት ቤት ሲሄድ በድንጋጤ አንድ ተመሳሳይ ፊት ያላቸው ሦስት ልጃገረዶች አየኋቸው ነው የሚለው ። መንትያዎች ተመሳሳይ መልክ ስለነበራቸው እያንዳንዳቸውን ተዘበራረቁበት አንዳቸውን ከአንዳቸው የሚለይበት ልዩ የሆነ ነገር አልነበረውም ። የሄደበትን አላማ ረስቶት በመገረም ከመካከላቸው መጀመሪያ ያውቃት የነበረችውን ናታሊ የትኛዋ እንደሆነች ነበር መጠየቅ የጀመረው ። ሶስቱ ልጆች የማይነጣጠሉ በመሆናቸው አንድ አይነት ሰው ማግባት እንደሚፈልጉ ምናልባትም በሂወት እስካሉ ድረስ አንድነታቸውን ወደ ፊት መቀጠል እንደሚችሉ ነበር የነገሩት ። ሶስቱም እህትማማቾች ሀሳባቸው አንድ አይነት ስልነበር ከዚህ ሰው ጋር በፍቅር ውስጥም ወደቁ ። በሀገሪቷ የመጀመሪያ ታሪክ የሰራም ይህ ግለሰብ የሚያስደንቀው ነገር መጀመሪያ ያውቃት ከነበረችው ውጭ ያሉት እህትማማቾች  ጸባያቸው ፡ ቁንጅናቸው ተመሳሳይ በመሆኑ አንዷን ብቻ መርጦ ለማግባት ተችግሮ ስለነበር ነው ሶስቶችን በአንድ ቀን ለማግባት የወሰነው ። ከልጅነታችን  ጀምሮ ሕይወታችን ተመሳሳይ ነው አሁንም ተመሳሳይ መሆን አለበት በማለት ነው እያንዳንዳቸው የሚናገሩት ። እህትማማቾችም መጀመሪያ ላይ እንቆቅልሽ ነበር የመሰለን ከግዜያት በኋላ ግን ምንም ነገር ሊያግደን አልቻለም፡ በአንድ ባል ተሳስረናል በማለት በደስታ ነው የተናገሩት ። መጀመሪያ ላይ ከሶስቱ ልጆች መካከል አንዷ ሁላቸውንም ማግባት እንዳለባቸው ስትነግረው ተደናገጠ፡ነገር ግን ቀድሞውንም ከሁላችውም ወዷቸው ስለነበር እቅዳቸውን ማቆም እና ማበላሸት አልፈለገም ነበር ። ሶስቶችን መንትያ ሴቶች በማግባቴ ልዩ እና ለእኔም የሚያስደንቅ ህልም የሚመልስ ነው ሲልም ይገልጸዋል ። ምንም እንኳን ሰዎች ለሶስት ሴቶች አንድ ባል መሆን እንደማይችል ቢያስቡም እነርሱ ግን ሁሉንም ነገር አንድ አይነት በሆነ መልኩ ማድረግ ይችላሉ። 

በሰርጋቸው ቀን እነዚህ ሶስት ሙሽሮች ዛሬ እንደምታዩት ደስ ብሎናል ፣ ምክንያቱም ሕልማችን የነበረው በምናገናው ባል አልመለያየት ነበር ለእርሱም ጸሎታችን ተሰምቷል በማለት ይገልጹታል ። ሉዊዞ ገና ልጅ እንደነበረ 3 ሚስት  ማግባት እንደሚፈልግ  ያስብም  ነው። እህትማማቾች  በበኩላቸው ለባላችንም ታማኝ ልንሆን የወሰኑ ሲሆን  እኔ ነኝ ፤ እኔ ነኝ ፤ አረ እኔ ነኝ ቀድሜ ልጅ የምወልድለት ሲሉም ተደምጠዋል ። በአንድ ጊዜ ለሶስቶች የጋብቻ ጥያቄ ያቀረበው ይህ ግለሰብ ሶስት እጥፍ የሆነ ግዴታ እንዳለብኝ ይሰማኝልም ይላል። የሉዊዞ የማግባት ውሳኔውን ያልተቀበሉት እና ያልተስማሙት ቤተሰቦቹ ከሌሎች ሰዎች ብዙ ቅሬታቸውን እና ትችቶችን ስለደረሳቸው በሰርጉ እለት ባይገኙም የቅርብ ጓደኞቹ ብቻ ነበር የተገኙለት ። ቤተተሰቦቹ መቅረት ምንም ያልተጸጸተው ሉዊዞ ከቀሩት የቤተሰቦቹ አባላት ውስጥ ባትስማማም እንኳን የተገነኘችው አንዷእህቱ ብቻ ናት ። ግለሰቡ እንደሚለው ከሆነ አንድ ነገር ለማግኘት የግድ አንድ ነገር ማጣት አለብን እኔም ይህንን ነው ያደረኩት ይላል ። በአፍሪካዊ ባህላችን ጋር የማይሄድ  ይህ ጋብቻ መጥፎ ቢሆንም አንዳቹ ተደስተውበታል አንዳንቹ  ደግሞ ተናደውበታል ይላል ። ሶትቶችንም በማግባቴ ደስተኛ ነኝ ፍቅር ገደብ የለውም በማለት የሚገልጽ ሲሆን ፤ወላጆቸ ውሳኔየን በመናቃቸው በሰርጌ አልተገኙም የደስታየ ተካፋይ አልሆኑም በማለትም ተናግሯል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *