አምስት የአለማችን ለማመን የሚከብዱ ረጃጅም ሰዎች – Top 10 Tallest Men on Earth
ሰዎች በተፈጥሮ የተሰጣቸውን ጸጋ በመጠቀም ወይንም ደግሞ አስገራሚ በሆኑ ስራወች ስማቸው በአለም የጊነስ ሪከርድ በመዝገብ በታሪክ ይቀመጥላቸዋል ። ተፈጥሮ የሰጣቸው የራሳቸው ውበት እና ማንነት የሚገልጹ ከመሆናቸውም በላይ በሀገራቸው ከዛም አልፎው በአለም ላይ እውቅናን በማግኘት የጸጋቸው ወይንም የሙያቸው ባለቤት ይሆናሉ ። በሌላ በኩል ደግሞ ከሌሎች ሰዎች በሚደርስባቸው ጫናወች ራሳቸውን በማግለል የብቸኝነት ስሜት ሲሰማቸው ራሳቸውን ዝቅ አድርገው እንዲያዩ ይገደዳሉ ። ውድ የሁሉ ዴይሊቤተሰቦች እንደምን ቆያቹህ ሰላምታችን በያላቹበት ይድረስልን ። በዛሬው ፕሮግራማችንም ለናንተ የያዝንላቹ ብዙ አስቸጋሪ እና ከባባድ ግዜያቶችን አሳልፈው እውቅናን ያገኙ 5 የአለማችን ረጃጅም ሰዎችን የምነግራቹህ ይሆናል አብራቹህ ቆዩ ።
1ኛ – ሱልጣን ኮሰን
ከ2009 ጀምሮ የጊነስ ሪከርድ ባለቤት የሆነው የቱርኩ ተወላጅ ሱልጣን ኮሰን የአለማችን አንደኛው ረጅሙ እና ግዙፉ ሰው ነው ። በቱርክ ውስጥ በሚገኝ የኩርድ ቤተሰብ አባል የተወለደ ሲሆን 2.8 ሴ.ሜ የሚረዝምም ነው ። ይህ ልዩ የሆነው የቁመቱ እና ግዙፈቱ ፒቱታሪ ጊጋንቲስም የተባለ በሽታነበር እድገቱ እንዲጨምር ያደረገው ። በወጣትነት እድሜው የእድገት ሆርሞኖቹን ከመጠን በላይ በማምረት ነበር ቁመቱ የረዘመው ። ይህ ቁመቱ አንዳንድ የዕለት ተዕለት ተግባራትን ለማከናወን አስቸጋሪ ስነበር ክራንች በመጠቀም ነበር የሚራመደው ። ኮሰን በሙያው ወይንም ደግሞ የሚተዳደረው በግብርና ስራ ሲሆን ከ2014 በፈረንጆቹ አቆጣጠር በኋላ Magic Circus of Samoa ውስጥ በመሳተፉ እና በተለያዩ ትርኢቶች ላይ በመገኘቱ ሂወቱ ተቀይሯል ። በተመሳሳይ በሀገራችን ኢትዮጲያ ምንም እንኳን እንደ አለማችን ረጃጅም ሰዎች እውቅና ባይሰጠውም ብዙወቹ ስለሱ ፕሮግራሞችን ሰርተው ህዝብ እንዲያውቀው አድርገውታል አርሶ አደር አቶ በርሄ ጋሹ ረጅሙ ያላቸው ናቸው ። የ35 አመት እድሜ ያለው ይህ ግለሰብ 2.50 ሴ.ሜ ቁመት የሚረዝም ትልቅ ያለው ሲሆን በርሱል ልክ የሚሆን ጫማ ባለማግኘቱ ላለፉት 35 አመታት ያክል ጫማ አላደረገም ነበር ። የቁመት ባለጸጋው አርሶአደር ብርሄ ከቅርብ ግዜያት ያክል የእርሱን ችግር ያዩ ሰዎች እርዳታወችን እና በማድረግ አድርገውለታል።
2ኛ- ብራሂም ተኪዩላህ
ይህ የአለማችን ሁለተኛ ረጅሙ ሰው ሲሆን 2 .46 ሴ.ሜትር ወይንም ደግሞ 8 ጫማ ከአንድ ኢንጭ የሚረምዝም ምሮኳዊ ነው ። 13 ዓመት ከሞላው በኋላ እያደገ በመሄዱ ሰዎች እንኳን በእሱ ቁመት መጨመር እንዲጨነቁ አድርጓቸዋል። ይህ በተፈጥሮ የተሰጠው ቁመት እውቅናን እንዲያገኝ ያደረገው ከመሆኑም በላይ የአለም የጊነስ ሪከርብ ባለቤት እንዲሆንም ረድቶታል። በ18 አመቱ ታኪዮላህ ለየት ባለው ቁመቱ ህክምና ሂዶ በመታየቱ በአንጎሉ ውስጥ የሆርሞን ዕጢ ነበር የተገኘበት ። በተሳካ ሁኔታ ቀዶ ጥገናም ተደረገለት ፡ እብጠቱ ተወገደለት፡ በደሙ ውስጥ ያለው የሆርሞን መጠንም ወደ ጤናማ ሁኔታ ተመለሰለት ። አሁን ከፈረንሳይ ዜግነት ያገኘ ሲሆን ከፓሪስ በስተ ሰሜን 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው ሴንት-ፖል የመዝናኛ ፓርክ እየሰራ የሚገኝም ነው ።
3ኛ- ሞርተዛ መህርዛድ ሴላጃኒ
የኢራን ተወላጅ የሆነው የአለማችን ሶስተኛው ረጅም ሰው ሲሆን 246 ሴ.ሜ ወይንም 8 ጫማ 1 ኢንች የሚረዝምም ነው ። ይህ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን እና ዝናን እንዲያኝ ያደረገው የቁመቱ መርዘም በ16 አመቱ ነበር ማደግ የጀመረው ። እ.ኤ.አ.በ 2016 በሪዮ ጨዋታዎች ላይ የመረብ ኳስ ጨዋታ ላይ ከተሳተፈበት ጊዜ ጀምሮ በታሪክ ከፍተኛው የፓራሊምፒክ ሻምፒዮን ማግኘት የቻለ ሲሆ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸልሟል ፡እውቅናንም ማግኘት ችሏል ። በአሁኑ ጊዜም መህርዛድ በሀገረ ኢራን ላይ ቮሊቦል ቡድን ነው ። በተመሳሳይም በሀገራችን በኢትዮጲያ ረጅሙ ሰው ነገዎ ጅማ የሚባል ሲሆን በቁመቱ በስፋት መነጋጋሪያ ሆኖም ነበር ። ብዙ ጫናወች እና ግፊቶች ያስተናገደው ይህ ወጣት እድሜው 24 ሲሆን ቁመቱ 2.25 ሜትር የሚረዝም ነው ። ትምህርቱን እንኳን ለመማር ከባድ የሆኑ አስቸጋሪ ግዜያቶችን ያላለፈው ይህ ሰው ሚዲያ ላይ ከቀረበ በኋላም ነበር ሁሉም ነገር ወደ መልካም ነገር ተቀይሮ በአፍሪካ ድንቃድንው መዝገድ ላይ እንዲሰፍር የረዳው። በዘንድሮው አመትም በመጀመሪያው ዙር በአፍሪካ የድንቃድንድ መዝገብ ላይ የኢትዮጲያ ረጅሙ ወንድ በመባል እውቅና ተሰጥቶታል ።
4ኛ- ዣንግ ጁንካይ
የኢራን ተወላጅ የሆነው የአለማችን ሶስተኛው ረጅም ሰው ሲሆን 246 ሴ.ሜ ወይንም 8 ጫማ 1 ኢንች የሚረዝምም ነው ። ይህ በአለም አቀፍ ደበሀገረ ቻይና በሻንዚ ግዛት ውስጥ የሚገኘው ይህ አራተኛ ረጅም ሰው ሲሆን 2.42 ሴ ሜ ወይንም ደግሞ 7 ጫማ ከ11ኢንቺ የሚረዝምም ነው ። በኖቬምበር 2004 ጁንካይ የሀገሪቱ ረጅሙ ሰው ተብሎ የታወቀበት እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅናን የተሰጠበት ወቅትም ነበር ። ገና በ22 አመቱ ነበር ቁመቱ መጨመር የጀመረውም ይህም ደግሞ በፒቱታርይ እጢ በሽታ ምክንያት ነበር እድገቱ ሊጨምር የቻለው ። 1.65 ሴ ሜ ቁመት ያላትን ሴት በአግብቶ የሚኖርም ነው።
5ኛ- አሳዱላ ካን
በሀገረ ህንድ የሚገኘው ይህ አምስተኛው የአለማችን ረጅሙ ሲሆን 241 ሴ ሜት የሚረዝምም ነው ። አስገራሚው ነገርም ቤተሰቦቹም እያንዳንዱንዳቸው 5 ጫማ ወይም ከዚያ በላይ ርዝመት ያላቸው ስለሆኑ ርዝመት ለቤተሰቡ አዲስ አይደለም ። የካን ህይወት ችግር ስቃይ የተሞላበት ነበር ። መተዳደሪያንውን እንኳን ለማግኘት አድካሚ የሆኑ ስራዎች ሰርቷል ። በህንድ ውስጥ በቁመቱ ልዩ በመሆኑ ህይወቱ አስቻጋሪ በነበረበት ወቅት የሀገሪቱ መንግስት እውቅና በመስጠቱ እና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ አስደስተወታል። ወድ የተከበራችሁ የሁሉ ደይሊ ቤተሰቦች የዛሬውን ፕሮግራማችንን በዚሁ አበቃን ያላችሁን አስተያየት በኮሜንት አድርሱን ። በቀጣይ ለእናንተ የሚያስገርሙ የሚያዝናኑ እና ለናንተ ይጠቅማሉ ብለን የምናስባቸውን መረጃዎች ይዘንላችሁ እንቀርባለን እናመሰግናለን ።።