አለምን ያርበደበዱት የፑት አደገኛ ቀጣይ ትውልድ የጦር መሳሪያዎች
ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ያላቸው አሜሪካ እና የሩሲያ የኒውክለር ቦንቦችን ሊተኩሱ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ እየሰጡ ይገኛሉ ፡፡ በተለይ ደግሞ የሩሲያው ፕሬዝዳት ብላዲሚር ፑቲን በዚህ ጦርነት ውስጥ ኔቶ ከገባ የኒውክለር ቦንቡን ለመተኮስ እንዲዘጋጁ ለጦር ሀይሎች ትዕዛዝ ሰጥተዋል ፡፡ ይሄም አልበቃ ብሎ በቅርብ ቀናት መካከል በአለም ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የሃይፐርሶኒክ ክሩዝ ሚሳኤል በደቡባዊ ዩክሬን በሚገኙ የአውሮፕላን መጠገኛ ቦታዎቿን ተኩሳ ድምጥማጣቸውን አጥፍታለች ፡፡ በዚህም መሳሪያ መወንጨፍ ምክንያት አለም ወደለየት ጦርነት ልትንገባ ነው በሚል ስጋት ውስጥ ይገኛል ፡፡ በሌላኛው ፅንፍ ላይ ለቆመችው አሜሪካ ግን የዚህ የሃይፐር ሶኒክ ሚሳኤል መተኮስ ትልቅ ድንጋጤ የፈጠረ ነበር ፡፡ ዩክሬን እንደማንኛው ሚሳኤል ተተኩሶ መመከት እንደቻለች ስታወራ አሜሪካ በሰጠቻት ማብራሪያ ሃይፐር ሶኒክ መሳሪያ እንደሆነ ማወቅ ችላለች ፡፡ ሩሲያም አስረግጣ ተናግራለች ፡፡ የዚህ መሳሪያ መተኮስ አሜሪካ ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጥሮባታል ፡፡ ይህ ሃፐር ሶኒክ ሚሳኤል ሩሲያ እና ቻይና ጋር ታላቆቹ ሀገራት ተርታ ያሰልፋት ነበር ፡፡ ነገር ግን ይህን መሳሪያ ሁለት ጊዜ ሞክራው አልተሳካላትም፡፡ ታዲያ የሩሲያ ይሄን መተኮስ ምን ያህል አቅም እንዳላት ያስታውቃል። የፕሬዘዳንቷ ሰፐር ዌፐን እንመለከታለን ።
1- ሳርማት (SARMAT)
አር ኤስ 28 ሳማርት የብላስቲክ ሚሳኤል በምህፃረ ቃል አይ ሲ ቢ ኤም በመባል የሚጠራ ግዙፍ መሳሪያ ነው፡፡ የዚህ መሳሪያ ክብደት ከአስር ቶን በላይ ይሆናል፡፡ ከሳርማት በፊት ከነበሩት መሳሪያዎች አንፃር በሚሸፍነው ርቀት ከፍተኛ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ በዚህም እስከ 18ሺ ሺህ ኪሎ ሜትር የሆነን ርቀት ማካለል የሚችል ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሽርፍራፊ ሰከንዶች ውስጥ ጥቃት ሊሰነዝሩበት የሚችሉትን መመከት ይችላል ፡፡ በደቡባዊ ንቅፈ ክበብ አድርጎ የአሜሪካን ከፍተኛ የሚሳየል ጥቃቶችን የሚለዩ እና የሚከላከሉ ስርዐቶችም አለው። ወደፊት ትልቁን የአቫን ግሬድ ሚሳኤሎች መሸከም እንዲችል ታስቦ እየተሰራበት ነው፡፡ የዚህ የጦር መሳሪያ ከ2020 እስከ ከ2021 ባለው ጊዜ ሙከራዎችን ያደረገ ቭሲሆን በሚቀጥሉት አመታት ግላጋሎት ሊሰጥ እንደሚችል ይነገርለታል ፡፡
2 – አቫንግራድ (AVANGARD)
ይህ የሚሳኤል ሲስተም የድሮውን አርኤስ 18 ኤ እና አዲሱን ዩ 71 ኤች ጂ ቪ በጥምረት በማቀናጀት የተሰራ ነው፡፡ በዚህም ምከንያት እንደሌሎቹ የባለስቲክ ሚሳኤሎች አብዛኛውን ጊዜውን ከመሬት፤ ከአየር ክልል ውጭ የሚሳልፍ አይደለም፡፡ ግን አብዛኛውን ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት ከላይኛው የአየር ከፍል ያሳልፋል፡፡ በተመሳሳይ ፍጥነት በመታጠፍ ብቃቱ ወደ ኢላማው በመሄድ ከፍተኛ ጉዳት የማድረስ አቅም ያለው ነው፡፡የዚህ አቫንግራድ ሲስተም የተጀመረው በ2002 አ.ም በአሜሪካ እና በሩሲያ መካከል በተደረገው የፀረ – ባስቲክ ሚሳኤል ስምምነት በኃላ ነው፡፡ በ2010ዓ.ም በተካሄደው አብዛኛው ሙከራ ብዙም ሳይሳካለት ሳይሳካለት ቢቀርም በ2015 እስከ 2016 ባሉት አመታት ጥሩ ስኬት አሳይቶ በ2019 ወደ ስራ ገብቷል፡፡
3 – ፖዚዶን (POSEIDON)
ይህ መሳሪያ መኖሩ የታወቀው በ2015ዓ.ም በመከላከያ ሚኒስተሮች ስብሰባ ላይ በተገኘ ፎቶ አማካኝነት ነው፡፡ የኒውክለር መሳሪያዎችን የታጠቀው ሰው አልባ ከውሀ በታች ያለ መሳሪያ ነው፡፡ በምህፃረ ቃልም ዩ ዩ ቪ በመባል ይጠራል፡፡ ከዚህ መጠሪያው በፊት በምህፃረ ቃል ስታተስ 6 በመባል የሚታወቅ ነበር፡፡ ይህም በጣም ግዙፍ፣ ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ እና ፈጣን ነበር፡፡ ነገር ግን ከ2015 ዓ.ም በኃላ መኖሩ ስለታወቀ ወደ ፓዚዶን ወደሚል መጠሪያ ተቀይሮ ብዙ ማሻሻያዎች እንደተደረገለት ይነገራል፡፡በዚህም በውስጡ ህጋዊ መሳሪያዎችን እና የኒውክለር ጦር መሳሪያዎችን መያዝ የሚችል አቅም ያለው ነው፡፡ በዚህም በአየር ላይ የሚሄዱ መሳሪያዎችን እና በባህር ዳርቻ አከባቢ ያሉ የምሽግ ቦታዎችን እንዲሁም የግንባታ መሰረቶችን ማውደም ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በባህር ውስጥ ከአንድ ኪሎሜትር በላይ በመስጠም ሰው ከሚያንቀሳቅሳቸውየባህር አይሎች ደህንነቱ መጠበቅ ይችላል ፡፡ በኒውክልር የሐይል መንጭ ተደርገው የሚሰሩ ሰው አልባ ከውሀ ስር ለሚንቀሳቀሱ መሳሪያዎች መሞከሪያ ጣቢያነት ሊያገለግል ይችላል፡፡ እንዲሁም ለሩሲያ ባህር ሀይል በጣም ፈጣን እና ከለምንም መቆራረጥ ከወር እስከ አመት ድረስ መቆየት የሚችል በሰው የሚታዘዝ መርከብ ለመስራት የሚያስቸል እድል እንደለው ይነገርለታል፡፡ ከዛ በተጨማሪ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ከውሀ በታች ባሉ የመገናኛመንገዶች ላይ ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል የሚነገርለት መሳሪያ ነው፡፡
4 – ብሪቭስትኒክ (BUREVESTNIK)
መሬት ላይ ተደርጎ የሚተኮስ የኒውከለር ሀይል ያለው ክሩስ ሚሳኤል ነው፡፡ ለየት የሚያደርገው ነገር ያለገደብ መሄዱ እና በማንኛውም ጊዜ መተጣጠፍ የሚችል መሆኑ ነው፡፡ በአሰራር ሁኔታ ከአሜሪካው ቶምሀውክ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን በሚጠቀመው የፈሳሽ ነዳጅ ምክንያት እስክ 2500 ኪሎ ሜትር ያህል ብቻ መሄድ የሚችል ነው። ማንኛውም ፀረ -ሚሳኤል መሳሪያ ስርአቶችን አልፎ ማቆም የማይችሉት ነው ፡፡ ይህ መሳሪያ አሜሪካ ከ1950 ጀምሮ ብትሞክርም አልተሳካልትም፡፡ ሩሲያም ቡሪቭሰትኒክ በጣም በብዙ ፈተና እና ሙከራ ብታደርግም አልተሳካለትም ነበ ር፡፡ ከ2016 ጀምሮ እስክ 2018 ድረስ ብቻ አስራ ሶስት ሙከራዎቸን አድርጋል፡፡ በ2018 የተደረገው ሙከራ በአየር ላይ ሁለት ደቂቃ እና ከ 22 ሚይል በላይእንደሄደ ይነገርለታል፡፡ ከዛም በኦገስት የብሪቨስተኒክ ማብላያያ ጣቢያው ፈንድቶ አምስት ሳይቲስቶች ሞተውበታል፡፡ በአሜሪካ ትልቅ ስጋት ያደረበት ትልቁ ምክንያት አንደኛ የየትኛውም አለምን ክፍል መምታት መቻሉ፤ ሁለተኛውም ያልተገደበ አቅም መኖሩ እና ሶስተኛው የአንድን ክልል ሀገር አልፎ ከገባ ሀይለኛ ጥፋት እና ውድመት ማድረስ የሚችል ብቃት አለው፡፡ በርግጥ በሙሉ አቅሙ መስራት ባይጀምርም በጣቢያው ፍንደታ ለአሜሪካ ግን የማንቂያ ደውል ነበር፡፡
5 – ኪንዛል (KINZHAL)
ሀይፐርሶኒክ ክሩዝ ሚሳኤል ፡፡ ሃፐርሶኒክ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከድምፅ ከአምስት እጥፍ የሚፈጥን ማንኛውም ነገር የሚገልፅ ሲሆን ፤ በሰዐት ከስድስት ሺህ አንድ መቶ ሰባ አራት ኪሎ ሜትር ወይም ከዚያ በላይ የሚሄድ እጅግ ፈጣን መሳሪያ ነው፡፡ ይህ ከመሬት እስከ አየር ላይ መተኮስ የሚቻል ነው፡፡ወደ 480 ኪሎ ግራም የሚመዝን የኒውክለር ጭነት መያዝ የሚችል ነው፡፡ ፍጥነቱም ከድምፅ ከአስር እጥፍ በላይ ይሆናል፡፡ ኪንዛል በ4900 ኪሎ ሜትር በሰዐት እስከ 12 350 ኪሎ ሜት በሰዐት መብረር ይችላል፡፡እንዲሁም ማንኛውምን የመከላከያ ሲስተም አልፎ መሄድ እና ማጥቃት የሚችል ነው፡፡ ከዛ በላይ በማንኛውም መንገድ መከላከል እና መልሶ የማጥቃት እድል የማይሰጥ ነው፡፡ እንዲሁም በማንኛውም የበረራ ደረጃው ላይ በመተጣጠፍ መብረር የሚችል ነው፡፡በ2017 ዓ.ም ስራ ላይ እንንደዋለ የሚነገርለት ይህ መሳሪያ በርግጠኝነት መኖሩን ለማረጋገጥ እና አለምን ጉድ ያሰስባለው በዩክሬን መተኮሱ ነው፡፡
6 – ሲርኮን (TSIRKON)
መርከብ ላይ መሰረት አድርጎ የሚተኮስ ሀይፐርሶኒክ ፀረ -መርከብ ሚሳኤል ነበር፡፡ ሁለት አላማዎችን መሰረት አድርጎ የተሰራ ሲሆን ማንኛውም በምድር ላይ ያለ እና በባህር ላይ ያሉ ኢላማ ላይ መምታት ይቻላል፡፡ ፍጥነቱ ከተለመደው ሀይፐርሶኒክ ቢያንስም ከ500 -1000 ኪሎ ሜትር መከል ያሉ ኢላማዎችን መምታት የሚችል ነው፡፡ ግማሽ ባለስቲክ ሚሳኤል የመተጣጠፍ አቅም አለው፡፡