ኮሜዲያን ዶክሌ በአሳዛኝ ሁኔታ አረፈ – ሰይፉ ስለነበረበት የአእምሮ ችግር ተናገረ
በብዛት ዶክሌ በሚለው ቅጽል ስሙ የሚታወቀው ታዋቂው እና በብዙወቹ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ በአሳዛኝ ሁኔታ በተወለደ በ57 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል ። ዶክሌ ከዚህ በፊት ባጋጠመው የልብ ህመም ምክንያት በህክም እና ሲረዳ ቆይቶ ትናንት በአሜሪካ ዋሽንግተን ሜድስታር ሆስፒታል ውስጥ ማረፉን የሙያ አጋሩ አርቲስት ቴዎድሮስ ለገሰ ነበር የተናገረው ። ኮሜዲያን ዶክሌ በስራው ቅን እና ታዛዥ ባለሙያ ነበረ እያለ የሚገልጸው አርቲስት ቴዎድሮስ ከዚህ በፊትም ኢትዮጵያውያን ሲረዱት ቢቆይም ለሁለተኛ ጊዜ ታሞ ሆስፒታል ገብቶ ህክምና እንዲያገኝ ተደርጎም ነበር። ህይወቱን ግን ማትረፍ አልተቻለም ነበር ። አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ተወልዶ ያደገው ኮሜዲያን ዶክሌ በመድሐኒአለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርቱን ተከታትሏል ። የእሱንም ሆነ የቤተሰቡን ህይወት ለመምራት በመካኒክነት ትምህርት ቀስሞ ሲሰራ ቆይቷል ። በኋላ ላይ ግን የጥበቡን ዓለም በመቀላቀል በኮሜዲ ዘርፍ አንቱታን ያተረፈባቸውን በርካታ አይረሴ ስራዎችን ለመስራትም ችሏል ። ዶክሌ ላለፊት አስርት አመታት ያክል በኮሜዲያኑ ዘፍር አዝናዥ አስተማሪ እና ቁም ነገር አዘል የኮሜዲያን ስራወችን ሲያቀርብም ቆይቷል ። ዶክሌ ሀገራችን ካፈራቻቸው ብርቅየ እና ግንባር ቀደም ኮሜዲያኖች ውስጥ አንዱም ነው ። በስታንድ አፕ ኮሜዲ እጅግ በርካታ አጫጭር ቁምነገር አዘል ቀልዶችን በማቅረብ የሚታወቀው ኮሜዲያን ዶክሌ ፤ በሙሉ ጊዜ የፊልም ስራዎች ላይ በመሳተፍ ዕውቅናና ዝናን ያተረፈ ነበረ ። ለአብነትም የራስ አሽከር የሚለው ታሪክ ቀመስ ፊልም ላይ የላቀ የትወና ብቃት እንዳለ ማስመስከር ችሏል ። በስራ አጋጣሚ ከስምንት አመታት በፊት ወደ አሜሪካ አቅንቶ ኑሮውን በዚያው አድርጎ የነበረው ኮሜዲያን ወንድወሰን ብርሃኑ) ባለትዳርና የአምስት ልጆች አባት ነበር ። ለአድናቂወቹ ለወዳጆቹ መጽናናትን እንመኛለል ነፍስ ይማር
ጋዜጠኛ ሰይፉ ፋንታሁን ከዚህ በፊት የአእምሮ ህክምና አድርጎ እንደሚያውቅ ነበር የተናገርው ። በራሱ በፕሮግራም ላይ ጋብዞት ከነበረውን ዶክተር ጋር ለብዙ አመት የቆየውን የነበረውን ሚስጥሩን በራሱ ፈቃድ ይፋ ያደረገው ። አሞት የነበረውም በፊት ይሰራበት ከነበረው ሸገር ኤፍ ኤም ወደ ኢትዮ ኤፍ ኤም ከተዛወረ በኋላ ጭንቀት እና ፍርሀት ይሰማው እንደነበረ እንዲሁም በእንቅልፍ ማጣት ይቸገር እንደነበረ ነው ዶክተሩ የተናገረው ። በቃለመጠይቁ ላይ የሰይፉ የአእምሮ ሀኪም የነበረው ዶ/ር ዳዊት ህመሙ አዲስ ነገር ውስጥ ስንገባ ለመልመድ ከመቸገር የተነሳ የሚመጣ የአእምሮ መረበሽ (Adjustment disorder) እንደሆነም ነበር የነገረው ። ህመሙ ከታወቀ በኋላ የንግግር የስነልቦ እና ህክምና አድርጎ እንደተሻለው በቃለመጠይቁ ተገልጿል ። በህይወት ውስጥ ጫና ሲያጋጥም ጭንቀት ወይም መከፋት የተለመደ ነው ። ይሄ ጭንቀት ወይም መከፋት በተለምዶ ከሚጠበቀው ጊዜ በላይ ከቆየ ወይም መጠኑ ከሚጠበቀው በላይ ከሆነ Adjustment disorder(Situational depression) ይባላል ። Adjustment disorder የሚፈጥሩት ጫናዎች አንድ ጊዜ በድንገት የሚከሰቱ አሉታዊ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ ። ለምሳሌ ፍቺ ፣ የእሳት አደጋ፣ ከስራ መባረር ፣ አዲስ ስራ መጀመር ፣ ገቢዎች ግብር ሲቆልል የሚከሰት ነው ። ሌላ ጊዜ ደግሞ ጫና የሚፈጥሩት ነገሮች አብረው የሚቆዩ ሊሆኑ ይችላሉ ። ለምሳሌ ትዳር ውስጥ ያለ ጭቅጭቅ ፣ ነዝናዛ የሚያካትትም ነው ። ሰዎች Adjustment disorder እንዲያጋጥማቸው የሚያደርጉት መጥፎ ነገሮች ብቻ ሳይሆኑ ጥሩ ነገሮችም ሊሆኑ ይችላሉ ። ለምሳሌ ትዳር መያዝ፣ ድንገት ሀብታም መሆን፣ ሹመት የሚካተቱም ናቸው ። ሰዎች ጫና ሲያጋጥመን የምንሰጠው ምላሽ እንደ የመልካችን ይለያያል ። ለአንዳንዶች በጣም የሚያስጨንቃቸው በሌሎች አይን በጣም ቀላል ነው ። ይህንን የሚወስነው አስተዳደጋችን፣ የምንጠቀማቸው ራስን የመደለያ መንገዶች (Defence Mechanisms) ፣ ያለን ማህበራዊ ድጋፍ የሚጠቀሱ ናቸው ። የAdjustment disorder ህክምና በዋናነት የንግግር የስነ ልቦና ህክምና ሲሆን በጣም አልፎአልፎ ለጥቂት ቀናት ለእንቅልፍ የሚያግዙ መድሀኒቶች ሊሰጥ ይችላል። ሰይፉ ፋንታሁን ስለ አእምሮ ህክምና በግልፅ ነበር የተናገረው ። ብዙወቹ ሰዎችም ካንተ ምስክርነት ማግለል እና መድልኦን ፈርተው ሳይታከሙ በየቤቱ የሚሰቃዩ ወገኖቻችን የአእምሮ ህመም ማንም ላይ ሊከሰት የሚችል ውጤታማ ህክምና ያለው ነገር እንደሆነ እንደሚረዱ ተስፋ አለኝ የሚል ነው የተናገሩት ።