በጉማ አዋርድ ያልተጠበቀው ተከሰተ – ሳያት ተቃወመች – ሙሉ ፕሮግራሙ

 በሀገራችን ኢትዮጲያ በ2014 አ.ም ለስምንተተኛ ግዜ የተካሄደው የጉማ አዋር የሽልማት ስነ ስርአት ሰሞኑን በደማቅ ሁኔታ ነበር የተካሄደው ። በሽልማቱ ላይ ታዋቂ የሆኑ ቲክቶከሮች እና ሌሎች የኪነ ጥበብ ሰዎች የተገኙ ሲሆን ሲሆን በብዛት የተገኙት ለየት ባሉ ባሕላዊ እና ዘመናዊ አልባሳት ተውበው እና ደምቀውም ነበር ። በተለይ አንዳንዶች የለበሷቸው ለየት ያሉ አልባሳት አድናቆትን ሲያስገኝላቸው ነበር ። በዚህ የሽልማት ስነ ሰአርት ላይ እጂግ አስገራሚ የሆኑ የቀይ ምንጣፍ አለባበሶች ታይተውም ነበር።  በሀገራችን ኢትዮጲያ  ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት የሚዘጋጀው ጉማ ፊልም አዋርድ ጥሩ ብቃት የተሰሩ ፊልሞችን ፡ተከታታይ ድራማወችን ፡ የፊልም ማጀቢያ ሙዚቃወችን እንዲሁም ደግሞ ኮከብ የሆኑ አርቲስቶችን ክብር እና እውቅና መስጠት በየ አመቱ አላማውን አድርጎ እየሰራ የሚገኝም ነው ።

በቀጣይም ደግሞ ሰሞኑን በተካሄደው የጉማ አዋርድ የሽልማት ስነ ስርአት ላይ በኮከብነት የተሸለሙትን አሸናፊወች የምነግራቹህ ይሆናል ። በምን አለሺ መቲ ፊልም የአመቱ ምርጥ ተዋናይ አርቲስት አምለሰት ሙጨ ፡ በግዛት ፊልም  የአመቱ ምርጥ ወንድ ተዋናይ አርቲስት እንድጋ ሰው ሀብቴ ቴዲ ፡በእረኛየ ተከታታይ ድራማ የአመቱ  ምርጥ መሪ ተዋናይ አርቲስት ሳያት ደምሴ፡ በዘጠነኛው ሺ ሲትኮም ድራማ አርቲስት ወንድማገኝ ለማ ፡ በፍቅር ጥግ ፊልም    ምርጥ ረዳት ተዋናይ አርቲስት ሽመልስ አበራ ፡ በፍቅር ጥግ ፊልም  የአመቱ ምርጥ የፊልም ማጀቢያ ሙዚቃ ድምጻዊ  እሱባለው  ይታየው የዘንድሮው የጉማ አዋርሽ ተሸላሚ የሆኑ ኮከብ አርቲስቶች ናቸው ።

  የጉማ አዋርድ ሽልማት በራሷ ፍላጎት አልቀበልም  ያለችው አርቲስት ሳያት ደምሴ  ሽልማቱን  በትህትና  አልቀበልም ነው ያለችው። ውድድር  በመኖሩ ጥሩ የሰራን  በማበረታታት አጥብቄ አምናለሁ ግን ሰው ነኝ እና የራሴ  እሳቤ እና መንገድ አለኝ። ውድ የጉማ አዋርድ አዘጋጆች ለሁሉም ድርጂት በቅድሚያእንዳሳወኩት ሁሉ ለተከበረ ድርጂታቹህ በቅድሚያ እንዳሳወኩ ሁሉ ለተከበረ ድርጂታቹህ  ምንም አይነት የእጩነት እና የውድድር ክብር  መድረክ አልሳተፍም ብየ ቀደም ብየ  አሳውቄአለሁ ፡ሌላ የሚገባው የስራ አጋሬ መበርከት  ሲገባው ሽልማቱ  ለምን እንዲህ ማድረግ እንደተፈለገ አልገባኝም እኔ እና ህሌናየ ግን ከእውነተኛ አክብሮት ጋር ሽልማቱን አልቀበልም ነው ያለችው  ። በዚህ  ወደ ፊት  ለሚደረጉት ማንኛውም  የእጩነት እና የመድረክክብሮች አልሳተፍም ራሴን  አግልያለሁ ነው ያለችው።   

በሽልማት ስነ ስአቱም ላይ ብዙወችን ሰዎችአሳሳቢ የሆነውን ጉዳይ ድምጽ ያሰማችው አርቲስት ምን ለብሳ ነበር እና ስቶ የሚሊመፈክሮችን ይዛ ታይታለች። ይህች አርቲስት በመጀመሪያ በዚህ ትኩረት ሳቢበ ሆነው መርሀ ግብር ላይ ይህን አሳሳቢ ድምጽ ላይ ስላሰማች ምስጋና ይገባታል ። ምን ለብሳ ነበር? የሚል ነውርን መሸፈኛ ቃል አመራረጧ እጂግ ይደነቃል ።

ብዙዎች ተምረዋልና የሕግ አካል ናቸው የሚባሉት ጭምር በሴት ልጅ መደፈር ጉዳይ የሴቷ አለባበስን እንደ ምክንያት ሲያቀርቡ ይታያል ። አስገድዶ መድፈር ከስነልቦናዊ ህመም እንጂ ከሴቷ አለባበስ እና ገላዋ መገላለጥ ጋር ግንኙነት የለውም ። የመድፈር ዝንባሌ ያለው ወንድ ሴቷ ምንም ብትለብስ ባመቸው ጊዜ ድርጊቱን መፈጸሙ አይቀርም ። አራስ እና የ3 ዓመት ልጅን የሚደፍር ወንድ ምኗ ተገላልጦ ነው የትኛው ጡቷና ዳሌዋ ማርኮት ነው በማለትም ነበር ምን ለብሳ ነበር የሚለውን መከፈክር ከሌሎች በተለየ መልኩ በመድረኩ ላይ ያሳየችው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *