“በዘረኝነት ነው ሃጫሉ ያልተሸለመው” – የሳሮን አስገራሚ መልስ ስለለዛ ሽልማት – Saron Ayelegn – Leza Award 2022

በሀገራችን ላይ ያሉትን የኪነጥበብ ስራወችን እና የኪነ ጥበብ ሰዎችን ከግዜ ወደ ግዜ እያደገ እና እየተስፋፋ እንዲሄድ እና ለሚሰሩትን እንደ ማበረታቻ እና እንደ ማነቃቂያ እንዲሆናቸው የተመሰረተ ነው ለዛ አዋርድ ። ለተከታታይ ለስምንት አመታት ያክል እተከበረ እያለ በሀገሩቷ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ እና በወቅታዊ ችግሮች ምክንያት ለሁለት አመት ያክል ሳይከበር መቆየቱም ይታወቃል ። ይህንኑ ምክንያት በማድረግም ነበር ግንቦት 17 ቀን 2014 አ.ም በሂልተን ሆቴል ብዙ አንጋፋ እና ዝነኛ የኪነ ጥበብ ሰዎች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተከኙበት ለአስረኛ ግዜ ነበር የተከበረው ። በሁለት አመት ቆይታ ውስጥ ስራወችን ህብዝ የወደደለላቸው እና ያከበረላቸው እንዲሁም ደግሞ ምርጥ ምርጥ የተባሉ አርቲስቶች ተሸልመውበታል ። ሽልማቱ በሂልተን ሆቴል ከተጠናቀቀ በኋላ በርካታ ቅሬታዎች ተነስተውበታል ። በተለይ የአመቱ ምርጥ ምርጥ ድምጻዊ እና የአመቱ ምርጥ አልበም የህዝብ ምርጫ ተብሎ መስፈርት ተቀምጦ እያለ በህዝብ በከፍተኛ ድምፅ ሲመሩ የነበሩት ሳያሸንፉ ቀርቷል ነበር ያሉት ብዙወቹ ። ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ የሚሉ ቅሬታዎች ይዘውም ለአዘጋጆቹ ነበር የተናገሩት መልሱ ምን እንደተባሉ ባናውቅም ። አንዳንድ መረጃወች እንደሚሉት ከሆነ ሽልማቱ እና በተመልካች በአድማጭ ድምጽ ያሸነፈው አልነበር በማለት ውዝግቦችን አስነስቷል ። አንዳንዲቹ እንዳው ብዙ ድምጽ ያገኙትየት ናቸው የሚሉም አሉ ። በተለይም ደግሞ ነፍሱን ይማረወና የአርቲስት ሀጫሉ አልበም ለምን አልተሸለመም የሚለው ነበር በብዙወች ዘንድ ተጭበርብሯል በማለት በስፋት አነጋጋሪ ጉዳይ የሆነው ።

Maal Mallisaa አልበም Spotify ቁጥር አንድ Streaming Album ሆኖ የቀረበ ሲሆን በ15 ሃገራት የሙዚቃ ቢልቦርድ ላይ አንደኛ ነበር ። በITunes ላይ የመሪነት ስፍራን የያዘ አልበም ነው ። በአለማችን ግዙፉ የሙዚቃ ሽልማት ስነ ስረአት ላይ በGrammy Award የመታሰቢያ ስፍራ የተሰጠው ሲሆን በለዛ አዋርድ ግን ሳይሸለም በመቅረቱ ብዙወችን ውዝግብ ውስጥ እንዲገቡ ያደረገም ነው ። የሀጫሉን ዘፈን ውድድር ውሰጥ ማስገባት ለራሱ እውቅና ለማግኘት እንጂ ሀጫሉን ቮት ያደረጉ የህዘብ ድምፅ ለማክበር አይደለም ይላሉ አንዳንዶቹ ። በዚህ ምክንያትም ነበር አርቲስት ሳሮን አየልኝ የራሷን መልእክት በማህበራዊ ሚዲያዋ ላይ ያሰፈረችው ። በሽልማቱ ላይ ባለቤቱ ተገንታ ስለነበር ቀና በይ ቀን አለ በማለት መልእክቷል የጀመረችው ። እስኪ እናንተ እንኳን እች ልጅ ስታዩ ልባቹሁ የማያዝን እና ስብር የማይል ማን አለ በእውነት ሴት እህት ሆነ እናት የላቹሁም ወይ ሀጫሉ በህይወት የለም ነብስ ይማር ። ነገር ግን በአድማጭም ሆነ በተመልካችም እሱ ቀዳሚ ነበር ሽልማቱ ይገባው ነበር ብላለች ። አንዳንዴ ከዘር ከጥላቻ እንውጣ እና ስለእውነት እናውራ እኔ በበኩሌ በጣም አዝኘአለሁ እንዲሁም እንኳን አልተገኘሁ በማለት የተስማኝን ለመግለፅ እወዳአለሁ ። አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ከዚህ የተሻለ አዋርድም ሽልማትም ይገባው ነበር ። እንዲሁም ሽልማቱ ስለሚገባቸው ሽልማቱን ለወስዱ ለሙያ ባልደረቦቼ እና ለጎደኞቼ እንኳን ደስ አላቹሁ ለማለት እወዳለሁ ኢትዮጵያውያን እና ህዝቦቿን እግዚአብሔር ይባርክ ብላለች ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *