ለዛ አዋርድ ፕሮግራም – ያልተጠበቁ አርቲስቶች ተገኙ – አስገራሚ አለባበስ – Leza Award Ethiopia 2022

https://youtu.be/gVuyX9V17Gc

ሰሞኑን በደማቅ ሁኔታ የተካሄደው የለዛ አዋርድ ሽልማት ታዋቂ እና አንጋፋ የጥበብ ሰዎች ምሽቱንም ያደመቁትን ሲሆን ከፊልም ስራ የራቀችው ተዋናይት ማህደር አሳፈም ተገኝታለች ። የኪነጥበብ ሰዎችን በአመት አንድ ጊዜ በህብረት ተገናኝተው የሆድ የሆዳቸውን እየተጨዋወቱ እዲያመሹ ፣ ለአዲስ መጪዎቹ ልምድ ማግኛ እንዲሆናቸው ፣ ለአንጋፋዎቹም ደግሞ ትውልድ ማፍሪያ እንዲሆን ታስቦም ነው ።

ተከስቶ በነበረው የኮሮና ቫይረስ እንዲሁም ደግሞ ሀገሪቷ ሰላሟን  ባጣችባቸው በሁለት አመታትን ያክል ሳይካሄድ ቆይቶም ነበር ። ሁለት አመታት በመዘግየቱ ምክንያት በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 የለዛ አድማጮች ምርጫ ሽልማት ስነስርአት ተብሎ በተሰጠው ስያሜ ሰሞኑን  ግንቦት 17 ቀን ወር 2014 ዓ.ም ላይ የሂልተን ሆቴል  ለአስረኛ ግዜ በደማቅ ሁኔታ ነው የተከበረው  ። ሽልማቱ ደግሞ በብዙ የስራ ዘርፎች ላይ መሰረት  ያደረገም ነበር ። ለዛ በቅን ሃሳብ ተነስቶ፣ በመልካም አድራጊ በጎ ሰዎች ጎልብቶ ፣ በብዙ የኪነ  በጥበብ ሰዎች ደምቆ  እስካሁን ድረስ ያለ የቆየም ነው ።

አንጋፋ የኪነ ጥበብ ሰዎች ፡ ተጋባጅ እንግዶች እና ሌሎችን በተገኙበት ሲሆን  አንድም የሀገራችን የጥበብ ሰው የቀረ የማይመስልበት ውብ እና ደማቅ ምሽትም ነበር ። በምሽቱ በተካሄደው በለዛ አዋርድ የሽልማት ስነ ስራት ላይ የተሸለሙትን እንመለከታለን። በ ምርጥ የተከታታይ ድራማ ተዋናይ ዘርፍ ሚሊዮን ብርሃኔ(ጩቢቲ) አሸናፊ ሆኗል ። በመድረኩ እንዲህ አለ፣ አንድ ምስጋናና አንድ ይቅርታ አለኝ።

ለዛ አዋርድ ፕሮግራም – ያልተጠበቁ አርቲስቶች ተገኙ – አስገራሚ አለባበስየማመሰግነው የድንግል ማሪያምን ልጅ፣ ያባቶቼን የነ የተክልየን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን ፤ ይቅርታ የምለው ባለፉት አመታት በኢትዮጵያ ይሄ ሁሉ መጎሳቆልና ፍዳ እየደረሰበት ላለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ምንም መናገር ባለመቻሌና እስካሁን መተንፈስ ባለመቻሌ ይቅርታ እጠይቃለ ነበር ያለው ። በዚህ የአመቱ ምርጥ አዲስ ድምፃዊ  ዳዊት ጽጌ ፡ የህይወት ዘመን ተሸላሚ  የሆነችው ደግሞ  ድምጻዊ  ሰላም ስዩም ፡ የአመቱ ምርጥ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ከእረኛየ ተዋንያን ድርብ ወርቅ  ሰይፉ ፡ የአመቱ ምርጥ የሙዚቃ ቪድዮ ቆሜ  ልመርቅሽ የአርቲስት ዶክተር  ጥላሁን ገሰሰ ፡ የአመቱ ምርጥ ወንድ ተዋናይ አማኑኤል ሀብታሙ ከእንሳሮ  ፊልም ፡ የአመቱ ምርጥ ዘፈን ወይ ልምጣ ወይ ምጣ  ድምጻዊት መሰሉ ፈንታሁን  የአመቱ ምርጥ ተዋናይት መስከረም አበራ ከእንሳሮ ፊልም ፡ የአመቱ  ምርጥ ነጠላ ዜማ አሸናፊ ድምጻዊ  ሮፍናን አሸናፊ ሆኗል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *