በአሳዛኝ ሁኔታ ከፎቅ ወድቃ የሞተችው ሙሽሪት እና ምክኒያቱ

ፍቅር በእያንዳንዱ ሰዎች ውስጥ ያለ ፍጹም ሰላማዊ እና የተረጋጋ ሀይል ሲሆን ጥንዶች ምቹ የሆኑ ባህሪወቻቸውን ካሳዩ ቀጥይ ግዜያቶቻቸውን ስኬታማ በሆነ መገድ ያሳልፋሉ ። የሚፈልጉትን ግንኙነት ግልጽ በሆነ መንገድ ካወቁ ፡ ጥሩ ግዜያቶችን አብረው በማሳለፍ ከቻሉ ፡ በችግር ግዜ አብረው ከተጋገዙ እና እርስ በእርስ ከተረዳዱ መልካም የሆነ ግንኙነት ይኖራቸዋል ። መሰረቱን የጸና እና ግንጽኝነት የተሞላ ግንኙነት ከሆነ ወደ ትዳር ከዛም አልፎ ትልቅ እና ደስተኛ የሆነ ቤተሰብ መመስረት ይችላል ። ግን ደግሞ አለመግባባት እና ግልጸኝነት የጎደለው ግንኝነት ከሆነ የስነ ልቦና ጉዳት ከዛም አልፎ ሂወትን እስከማጣት የሚያደርስ ነው ። በዛሬው ፕሮግራማችን ለናንተ የያዝንላቹ የብዙወችን ልብ የሰበረው አሳዛኝ ነገር አራት አመታትን ያክል   የቆየችውን እጮኛዋን ለማግባት እየተዘጋጀች እያለ በሰርጓ ማግስት በተፈጠረው አልመግባባት ምክንያት ሂወቷን ስላጣችው ሙሽራዋ ሀና የምነግራቹህ ይሆናል አብራቹን ቆዩ ።        

ለሰው ልጅ ጥሩ ማድረግ ባንችል አንኳ የውሸት ተስፋ በመስጠት ሂወታቸውን እንዲያጡ ምክንያት እየሆነም ነው ።       አንዳንዶቹ ሰዎች ብዙ የመናገር እና የማሳመን ችሎታ ባለው ምላሳቸው የሰዎችን ልብ ይሰብራሉ ፡ሂወታቸውን እንዲያጡ ያደርጋሉ ወይንም ደግሞ በሱስ ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋሉ ። በተለይም ደግሞ በጓደኝነት እና በእጮችነት ግዜ የመረጧቸውን ሰዎች ለማሳመን እና ወደ ራሳቸው እንዲመጡ ብዙ ነገሮችን በመጠቀም በትዳር አብሮ ለመኖር ይወስናሉ ። ሰሞኑንም አገባሻለው ብሎ ስትዘገጃጅለት የነበረው ሰውዬ ኢንጂነር ሲሆን ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነው ። ሚስቱም ኢንጅነር ናት ። ኑሮውን በጅማ ከተማ ያደረገው ይህ ግለሰብ ከዚህች ልጅ ጋር የፍቅር ግንኙነት የጀመረው ከ4 አመት በፊት ነበር ። የዩኒቨርስቲይ ተማሪ እና  የ25 አመት ወጣትም ነበረች ። ከዚህ በፊት በነበሩት ቀናቶች ብራይዲያሉዋን አክብራ ነበር ። ከእጮኛዋ ጋር ለመጋባት ስላሰቡ አዲስ አበባ በመምጣት ለሰርጋቸው የሚያስፈልጋቸው እቃዎች ለመግዛት በአንድ ሆቴል ላይ 8ኛ ፎቅ ማረፊያቸውን አደረጉ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ነበር መረጃውን ያስታወቀው ።  በወቅቱ አብረው በነበሩበት ሆቴል በዚህ ጉዳይ ይጨቃጨቃሉ ጭቅጭቁ እየጨመረ ሲሄድ ከነበሩበት ሆቴል ጥሏት ይወጣል። በዚም አጋጣሚ በ15 ደቂቃ ልዩነት ውስጥ ራሷን ያጠፋቸው ። ይህ ድርጊትም ብዙወቹን ያሳዘን  እና ልብ የሰበረ ጉዳይም ነው። 

ይህቺ ልጅ ይሄንን ውሳኔ የወሰነችው ነገ ሰዉ ምን ይለኛል ፡ ድግስ ተደግሶ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ በሚል እሳቤ ይሆናል ። አንዳንድ ክፉ ሰውች ስንቱን በምላላሳቸው ገድለዋል ስንቱንስ ከመንገዱ አስቀርተውታል ያለ ስማቸውስ ስም እየሰጡ ስንቶችን ያሳበዱ እና ያናደዱዱ ሰውች ይኖር ይሆን ።  

 

     

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *